የክፍያ ቼክ፣ W2 እና የቅጥር ማረጋገጫ

የእርስዎን W2 ኦንላይን ማግኘት

 • ወደ https://my.adp.comይሂዱ
 • “አሁን ይመዝገቡ” ላይ ጠቅ ያድርጉ
 • የምዝገባ ኮዱን ያስገቡ፦ (HMS1-IPAY)
 • ስምዎን ያስገቡ እና W-2 አገልግሎቶችን እንደ አገልግሎት አድርገው ይምረጡ
 • የሚከተሉት መረጃዎች ለማረጋገጫ አላማዎች ያስፈልጋሉ፦
  • ሙሉ የህብረተሰብ ደህንነት ቁጥር SSN/SSA፦ ለምሳሌ 123456789 (ሰረዝ ሳይገባ)
  • የሰራተኛ መታወቂያ ቁጥር፦ ለምሳሌ 0123456 ሰባት አሃዞች ከዜሮ የሚጀምሩ
  • ከክፍያ ዝርዝሩ (paystub) የላይኛው መሀል አካባቢ የሚገኝ
  • የኩባንያ ኮድ፦ WHG (ሁሉንም በካፒታል ሌተር)
  • የሰራተኛ ዚፕ ኮድ – ከ 12/31/2019 በኋላ ፋይል ላይ ያለ ዚፕ ኮድ
  • የግብር አመት፦ 2019

የክፍያ ዝርዝርዎን (Paystub) ቅጂ መጠየቅ

 • የክፍያ ዝርዝርዎን (Paystub) ቅጂ መጠየቅ ከፈለጉ፣ እባክዎን ወደ HRHelpDesk@hmshost.com ኢሜይል ይላኩ
 • እባክዎን የሰራተኛ መታወቂያ ቁጥርዎን እና የክፍያ ዝርዝርዎን (Paystub) ቅጂ መጠየቅ የሚፈልጉለትን የፔይሮል ክፍለ ጊዜ ያቅርቡ።

የጠፋ የክፍያ ቼክዎ ላይ ክፍያን ማስቆም

 • የጠፋ ቼክ ካለዎት፣ እባክዎን የክፍያን ማስቆም ጥየቃ ቅጽ (PDF) ሞልተው ይጨርሱ
 • ባለው ነባራዊ ሁኔታ ምክንያት የኖታሪ ፊርማ መጠበቅ ለደህንነት አስተማማኝ እንዳልሆነ እና የሚታሰብ እንዳልሆነ እንረዳለን፣ ይሁንና ግን እባክዎን ከእርስዎ አካባቢያዊ የሰው ሃብት አስተዳደር ጋር ጥያቄውን ለማጽደቅ ይስሩ። ቅጹን እስከሚቻለው ድረስ በሙሉ መሙላትዎን አይዘንጉ። የቀረ ማንኛውም መረጃ በእርስዎ አካባቢያዊ የሰው ሃብት አስተዳደር መጠናቀቅ ይችላል።
 • ክፍያ ማስቆሙ ከጸደቀ በኋላ ከዑድት-ውጪ (off-cycle) ቼክ እንሰጣለን።
 • እባክዎን ተጨማሪ ቼክ እንዳይጠፋ ለመከላከል አድራሻዎ ትክክል መሆኑን ያረጋግጡ።

HMSHost ጋር ቅጥርዎን ማረጋገጥ

 • የ HMSHost ባልደረባዎች ቅጥርን እና ገቢን የሚያረጋግጡባቸው ሁለት አማራጮች አሉ፦
 • አማራጭ #1 – ቅጥርን እና ገቢን የሚያረጋግጠው አካል የሚከተለውን በማድረግ መረጃን በቀጥታ መጠየቅ ይችላል፦
  • www.theworknumber.comን በመጎብኘት
  • የእኛን አሰሪ ኮድ በማስገባት – 19413
  • የሚያጋግጡትን ባልደረባ የመጨረሻ ስም ማስገባት
 • አማራጭ #2 – የ HMSHost ባልደረባዎች የሚከተሉትን በማድረግ መረጃቸውን መድረስ እና ለአረጋጋጩ መላክ ይችላሉ፦
  • የሪፖርቱን ቅጂ ለመጠየቅ 866- 604-6570 ላይ በመደወል የሥራ ቁጥር የደንበኛ አገልግሎት ማዕከልን ማነጋገር
   ወይም
  • www.theworknumber.com መጎብኘት እና ወደ ሠራተኛ ክፍል መሄድ (በመለያ መግባት ያስፈልጋል)
  • እንደ አሠሪዎ አድርገው ‘HMSHost Corporation’ መምረጥ
  • በዌብሳይቱ ላይ ቀደም ብለው ተመዝግበው ካልሆነ፣ ‘Sign Up’ የሚለውን መምረጥ አለብዎ (ምዝገባውን ለማሟላት የመገኛ መረጃን፣ SSN#፣ እና DOB ለመስጠት ዝግጁ ይሁኑ)
  • ከተመዘገቡ በኋላ፣ ሪፖርቱን ወዲያውኑ እንዴት ማውረድ እንዳለብዎ መመሪያዎችን ለማግኘት እዚህ ላይ ጠቅ ያድርጉ