ስለ ጥቅማ ጥቅሞቼ

Hየተጠራቀመ የክፍያ ፍቃዴን መጠቀም ለማቆም የክፍያ ፍቃዴን ምርጫ እንዴት ነው የምቀይረው?

በ Furlough ጊዜ የክፍያ ፍቃድዎን መጠቀም ካልፈለጉ (አማራጭ 1)፣ ምርጫዎን ወደ አማራጭ 2 ለመቀየር እስከ ኤፕሪል 9 ድረስ 855-645-7268 ላይ (ረቡዕ፣ ማርች 25 በ12 pm ET ላይ የሚገኙ) መደወል አለብዎት። ከኤፕሪል 9 በኋላ፣ ምንም ዓይነት ለውጥ ማድረግ የማይችሉ ሲሆን የክፍያ ፈቃዱም ምርጫዎች እስከ የFurlough መርኃግብሩ እስከሚያበቃ ተፈጻሚ ሆኖ ይቆያል።  የክፍያ እረፍትዎን መጠቀም ለመቀጠል ከፈለጉ፣ ምንም ማድረግ አይጠበቅብዎትም።

የክፍያ ፍቃድን ከተጠቀምኩኝ፣ Furlough መርኃግብር ላይ ሳለሁ አዲስ የክፍያ ፍቃድ ማግኘቴን እቀጥላለሁ?

አዎን። አንድ ባልደረባ ሊያገኝ የሚችለው የፍቃድ መጠን በአገልግሎት አመታዊ ክብረ በዓል ውስጥ ጠቅላላ የተከፈሉት ሰዓታት (የተሰራባቸው ሰዓታት ሳይሆን) ላይ የተመሰረተ ነው።

Furlough ጊዜ ላይ የክፍያ እረፍት በገንዘብ ሊቀየር ይችላል?

አይ። የክፍያ እረፍት በFurlough ጊዜ ላይ በገንዘብ ሊቀየር አይችልም፣ እሱን መጠቀም የሚቻለው በFurlough ፕሮግራም ውሎቹ መሰረት ብቻ ነው።

በFurlough ጊዜ የበዓል ቀን ክፍያ አገኛለሁ?

አያገኙም። አለመታደል ሆኖ በFurlough ጊዜ የበዓል ቀን ክፍያ ተፈጻሚ አይሆንም።

በFurlough ላይ ሳለሁ ለሥራ አጥነት ማመልከት እችላለሁ?

አዎ። ወዲያውኑ ማመልከት አለብዎት። ለበለጠ መረጃ እባክዎን የስራ አጥነት ማመልከቻ ያስገቡ ክፍልን ይመልከቱ።

የጤና እና የደህንነት ጥቅማ ጥቅሞችን ምርጫ መለወጥ እችላለሁ፤ ወይም የጤና እና የደህንነት ጥቅማ ጥቅሞቼን በFurlough ላይ እያለሁ መሰረዝ እችላለሁ?

ብቁ የሚያደርግ የህይወት ክስተት ወይም አመታዊ ምዝገባ ካለ በስተቀር “ከግብር በፊት” የጤና እና የደህንነት ጥቅማ ጥቅም ሽፋንን መሰረዝ ወይም መለወጥ አይቻልም። በአሁኑ ጊዜ፣ የኮቪድ-19 Furlough በፌዴራል መንግሥት ብቁ የሚያደርግ የሕይወት ክስተት ተደርጎ አልተወሰደም። ብቁ የሆነ የህይወት ክስተት በተከሰተ በ 45 ቀናት ውስጥ የባልደረባ ጥቅማ ጥቅም ማዕከልን 1-877-454-4678 ላይ ማነጋገር አለብዎት።

“ከግብር በኋላ” የጤና እና የደህንነት ጥቅማ ጥቅም ሽፋን በየትኛውም ጊዜ በማንኛውም ምክንያት ሊሰረዝ ይችላል፣ ነገር ግን ሽፋን ከተሰረዘ በኋላ መልሶ ለማስቀጠል የጤና መግለጫ እንዲያገኙ ሊፈለግብዎ ይችላል። ሽፋንዎን ለመሰረዝ ጥያቄ ካቀረቡ፣ ያለ ሽፋን ያሳለፉት የመጀመሪያ ቀን ጥያቄ ያቀረቡበት ቀን ይሆናል። ሸፋኑ የሚሰረዘው ጥያቄ ካቀረቡበት ቀን በፊት ያለው እኩለ ሌሊት ላይ ነው። ሽፋንዎን ለመሰረዝ የባልደረባ ጥቅማ ጥቅም ማዕከልን 1-877-454-4678 ላይ ማነጋገር አለብዎት።

ከባልደረባ ጥቅማ ጥቅም ማዕከል በ HMSHost ባስመዘገቡት አድራሻ መረጃዎችን በ U.S. ፖስታ በቀጥታ ይቀበላሉ።

እባክዎ ሁሉንም መረጃዎች በጥንቃቄ ያንብቡ።

ይህን መረጃ በተመለከተ ማናቸውም ጥያቄዎች ካልዎት የባልደረባ ጥቅማ ጥቅም ማእከልን 1-877-454-4678 ላይ ደውለው ያግኙ። ተወካዮች እርስዎን ለማገዝ ከሰኞ እስከ አርብ ከ 9:30 am እስከ 5:30 pm ኢስተርን ታይም ይገኛሉ።

የእኔ 401k ላይ አሁንም አስተዋእጾ ማድረግ እችላለሁ?በአጠቃላይ፣ የትኛዎቹም የ 401k አስተዋእጾዎች በክፍያ ቼክ በኩል መምጣት አለባቸው። ክፍያ ለመቀበል የክፍያ እረፍት የሚጠቀሙ ከሆነ፣ ለ 401k አስተዋእጾ ማድረግ ይችላሉ። ካልሆነ ግን መለያዎ ንቁ ይሆናል ግን አስተዋጽዖዎች አይኖሩትም።አስተዋእጾዎችን ሙሉ ለሙሉ ማቆም ከፈለጉ፣ ይህንን ምርጫ መምረጥም ይችላሉ።401(k) እቅድ ላይ አስተዋእጾዎችን ማድረግ ወይም መቀየርን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ እባክዎን 1-800-835-5095 ላይ ወይም በ www.netbenefits.com በኩል የፊደሊቲ ኢንቨስትመንትን ያነጋግሩ።

የ 401k ብድሬ ምን ይሆናል?
ያልተከፈለ የ 401(k) የጡረታ ቁጠባ እቅድ ብድር ካለብዎ፣ የብድር መክፈያ ጊዜው እስከ 1 አመት ወይም ፈቃድ እስከሚያልቅበት ቀን ድረስ ይቋረጣል። የአርስዎ ሁኔታ ፈቃድ የተሰጠው እረፍታዊ ቀሪ ብሎ ማሳየት አለበት። ሁኔታዎ ፈቃድ የተሰጠው እረፍታዊ ቀሪ ብሎ የማያሳይ ከሆነ፣ በተከታታይ 90 ቀናት ውስጥ ክፍያ ካልተፈጸመ ብድሩ ያልተከፈለ ተደርጎ ይቆጠራል። የብድር ክፍያን በቀጥታ ስለመክፈል ላይ መረጃ ለማግኘት እባክዎን የፊደሊቲ ኢንቨስትመንትን 1-800-835-5095 ላይ ያነጋግሩ።

የሰራተኛ እገዛ ፕሮግራምን ማግኘት እችላለሁ?

አዎን። የእኛ የሰራተኛ ድጋፍ ፕሮግራም (EAP) በሦስተኛ ወገን ሚስጥራዊ አገልግሎት አቅራቢ የሚተዳደር ሲሆን በማናቸውም የግል ህይወት ችግሮች እና የባለሙያ መመሪያ በሚፈልጉ ሁኔታዎች ላይ በጣም የሚጠቅም እና ሚስጢራዊ የሆነ ግብዓት ነው። እገዛ ለማግኘት፣ እባክዎን ፈርስት አድቫንቴጅን 1-800-935-9551 ላይ ያነጋግሩ።.